አዳዲስ ዜናዎች

ለወልቃይት አካባቢ በጀት እንዲለቀቅ ጥያቄ ቀረበ

የአማራና የትግራይ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ የሚያነሱበት ለወልቃይት አካባቢ በጀት እንዲለቀቅ፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት ጥያቄ አቀረቡ፡፡ አባላቱ ጥያቄውን ያነሱት የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ፣ የ2016 ዓ.ም. የፌዴራል መንግሥት ረቀቂ በጀት ለምክር ቤቱ ሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ባቀረቡበት ወቅት…

የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት የአገሪቱ የሰላም ሁኔታ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል አለ

የአገሪቱ የሰላም ሁኔታ የከፋ ቀውስ ውስጥ መሆኑንና አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን፣ የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አስታወቀ፡፡ የጋራ ምክር ቤቱ ይህንን ያስታወቀው ግንቦት 24 ቀን 2015 ዓ.ም. ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የደረሰባቸውን ውሳኔዎች አስመልክቶ፣ ዓርብ ሰኔ 2 ቀን 2015 ዓ.ም. በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡

ለመጪው ዓመት በቀረበው በጀት ለካፒታል ወጪ የተመደበው ገንዘብ ማነስ በፓርላማ ጥያቄ አስነሳ

በሚኒስትሮች ምክር ቤት ፀድቆ ለፓርላማው በተመራው የ2016 ዓ.ም. በጀት፣ ለካፒታል ወጪዎች የተመደበው ገንዘብ ማነስ በፓርላማው ከፍተኛ ጥያቄ አስነሳ፡፡ የገንዘብ ሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሽዴ ሰኔ 1 ቀን 2015 ዓ.ም. ረቂቅ በጀቱን አስመልክተው ባቀረቡት ማብራሪያ፣ ከቀረበው 801.65 ቢሊዮን ብር ውስጥ 370 ቢሊዮን ብር ለመደበኛ ወጪ፣ 203 ቢሊዮን ብር ለካፒታል ወጪ፣ 214 ቢሊዮን ብር ለክልሎች ድጋፍ፣ እንዲሁም 14 ቢሊዮን ብር ለዘላቂ ልማት ግቦች ማስፈጸሚያ ድጋፍ በፓርላማ ተደልድሎ ቀርቧል፡፡

One thought on “አዳዲስ ዜናዎች

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *